Sidebar

 

የአገሪቱ ህገ መንግሥት አንቀጽ 5፣ ቁጥር 2፣ “አማርኛ የፌዴራሉ መንግሥት የሥራ ቋንቋ ይሆናል” ሲል፤ እንደዚሁም መንግሥት 1994 እኤአ ያወጣዉና፣ አሁንም ድረስ በትምህርት ሚኒስቴር ድረ-ገጽ ላይ የሚገኘው፣ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ቁጥር 3.5.4፣ አማርኛ ቋንቋ ለአገራዊ ተግባቦት በትምህርት ቤቶች እንደ አንድ የትምህርት አይነት መሰጠት እንዳለበት ይደነግጋል።1

 

የአገሪቱ ህገ መንግሥት አንቀጽ 5፣ ቁጥር 2፣ “አማርኛ የፌዴራሉ መንግሥት የሥራ ቋንቋ ይሆናል” ሲል፤ እንደዚሁም መንግሥት 1994 እኤአ ያወጣዉና፣ አሁንም ድረስ በትምህርት ሚኒስቴር ድረ-ገጽ ላይ የሚገኘው፣ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ቁጥር 3.5.4፣ አማርኛ ቋንቋ ለአገራዊ ተግባቦት በትምህርት ቤቶች እንደ አንድ የትምህርት አይነት መሰጠት እንዳለበት ይደነግጋል።1

በተጨማሪም ትምህርት ሚኒስቴር ለረጅም ጊዜ ያስጠናዉና በብዙ ባለሙያዎች የተመራው ጥናት ለአገራዊ መግባቢያነት አማርኛ በአጠቃላይ በአገሪቱ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንደ አንድ የትምህርት አይነት ተጠናክሮ መሰጠት እንዳለበት ምክረ-ሃስብ አቅርቧል።2

(ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ። )

 

ለብዙ ኢትዮጵያዉያን ግልጽ ባይሆንም፣ ከአለው ህገ መንግሥት ወይም ትምህርት ሚኒስቴር ካስጠናው የትምህርት ፍኖተ ካርታ ፍጹም ተቃራኒ የሆነና፣ አማርኛን እንደ ትምህርት አይነት በኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች መሰጠት እንዳለበት የማይጠቅስ፣ ስርዓተ-ትምህርት በትምህርት ሚኒስቴር ተነድፎ  ከመስከረም 2015 ዓ/ም ጀምሮ በአገሪቱ  ተግባራዊ እንደሆነ በትምህርት ሚኒስቴር ተገሌፁአል ። እንዲሁም ይህን አገራዊ ቋንቋን አስመልክቶ ያወጣውን ፖሊሲ በህግ ለማጽናት መንግስት አጠቃላይ የትምህርት አዋጅ (ረቂቅ) የሚል በድብቅ እያዘጋጀ እንደሆነ ግልጽ ሆኗል። 

ይህንም አሳሳቢ ጉዳይ አስመልክቶ፣ በ People to People (P2P) Inc. እና Global Ethiopian Scholars Initiative (GESI) በተሰኙት ድርጅቶች በጋራ የተዘጋጀ፣ በዉጭና በአገር ዉስጥ የሚኖሩ ምሁራንን ያሳተፈ ሙያዊ ዉይይት ታኅሣሥ 1 ቀን 2015 ዓ/ም ተካሂዷል። በዉይይቱ ላይ የትምሀርት ሚኒስቴር ተወካይ እንዲገኙ ተጋብዞ አወንታዊ ምላሽ አልተገኘም።  የትምህርት ፍኖተ ካርታዉን ካጠኑት ባለሙያዎች ዉስጥ እንዲገኙ ያደርግነው ሙከራ አልተሳካም።

የተካሄድነዉን የምሁራኑን ወይይት ተከትሎ የተደረሰበትን ዉጤትና ምክረ ሃስብ ከዚህ ጋር በተያያዘው ጋዜጣዊ መግለጫ አቅርበናል። 

ዉይይቱን ላልተሳተፋችሁ፡ ቪድዮዎቹ ዩቲዩብ ላይ ይገኛሉ፤

በኢትዮጵያ የጋራ መግባቢያቋንቋን የሚያዳብር ስርዓተትምህርት አስፈላጊነት 

ክፍል1   https://www.youtube.com/watch?v=zmemlQs5h_k

በኢትዮጵያ የጋራ መግባቢያ ቋንቋን የሚያዳብር ስርዓተትምህርት አስፈላጊነት 

ክፍል2  https://www.youtube.com/watch?v=TzR7aIxwuS0

Deliberate Destruction of Museum, Hospitals, Schools, and Hotels. (2)

Haile Selassie The Pillar of a Modern Ethiopia